ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪፖርቱ ኢህአዴግ ምርጫውን ለማሸነፍ መልካም እድል መኖሩን ጠቅሷል።
ኢህአዴግ መንግስት መሆኑና የመንግስትን ንበረቶችና ጽህፈት ቤቶች መጠቀሙ እንዲሁም በቅስቀሳ ወቅት አንድ ለአምስት በሚል አሠራር በተጠቀመበት የቅስቀሳና የማሳመን አሠራር በርካታ ድምፆችን ለመውሰድ የሚያስችል እድል መፍጠሩን በ2002 ቱ ምርጫ
ወቅት መታየቱን አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሚኒስትሮች ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።
በቅድመ ውጤት ትንበያው ኢህአዴግ በከፍተኛ ድምጽ ያሸንፋል የተባለ ሲሆን አሁን ባለው የከተማ ፖለቲካ ክፍተት ተቃዋሚዎች 25 በመቶ ወንበር ሊወስዱ ይችላሉ ብሏል፡፡ በምርጫው የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች በቁጥር በርካታ ከመሆናቸው በቀር፣ ከገዢው
ፓርቲ ጋር ሲነጻጸሩ የሚወክሉትን መራጭ በአግባቡ ለመወከል የሚያስችልና በምርጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመወዳደር የሚችሉበት አቅም በእጅጉ ውሱን መሆኑ ለኢአዴግ ሰፊ የድል መሬት መፍጠሩን በሪፖርቱ ተመልክቷል። ለፖለቲካ ፓርቲዎች
የሚደረገው የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ አነስተኛ መሆን ለኢህአዴግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩም ተመልክቷል።
የፓርቲዎች የምርጫ ክርክር በመገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ሳይሆን በቴፕ ተቀርጾ በመተላለፉ የሚፈለገውን የቅንብር ስራ በወገንተኝነት እንዲፈፀም በር መክፈቱን፣ የሲቪል ማኀበራት በምርጫ አስተምህሮ እንዳይሳተፉ በምርጫ ቦርድ መከልከላቸው ተቃዋሚዎች የምርጫ ተሳትፎአቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዲገደብ ማድረጉም ተመልክቷል።
የግሉ ኘሬስ የምርጫውን ሂደት በመዘገብና ለሕዝብ የምርጫ ትምህርት በመስጠት ረገድ ከአዲስ አበባውጭ ባሉት ከተሞችና ገጠሮች የነበረው ተደራሽነት ውሱን መሆኑ ፣ ተቃዋሚዎች የምርጫ ትምህርቶቹ እና መልዕክቶቹ በተፈለገው ስፋት ለህዝቡ ለማድረስ አላስቻላቸውም።
በሪፖርቱ ኦሮምያ ክልል ዝዋይ፣ ሻሸመኔ ፣ አዳማ አካባቢዎች፣ በትግራይ ክልል ሽሬ እና ውቅሮ ማራይ አካባቢ፣ በአማራ ክልል ወልዲያ እና ቋሪት እንዲሁም በሐረርጌ በድጋሚ የምርጫ ካርድ የመውሰድ ሁኔታ መታየቱም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
የምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር ከ44,000 በላይ እንዲሆን መደረጉ ፣ በየምርጫ ጣቢያው አንድ ወኪል ለማስቀመጥ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ፣ ተቃዋሚዎች በሁሉም ምርጫ ጣቢያ ተወካይ ማስቀመጥ እንዳይችሉ በማድረጉ ለኢህአዴግ መልካም አጋጣሚ
ተፈጥሯል ብሎአል። ኢህአዴጋዊ በስጋትነት ያስቀመጠው፣ የዋጋአልባድምፅመበራከትን ነው። አንዳንድ መራጮች ሆን ተብሎ ሊያሰኝበሚችል መልኩ የድምፅ መስጫ ወረቀቱን ዋጋ-አልባ ያደርጉታል ሲል ሪፖርቱ አብራርቷል።