አቶ ስንታየሁ በደህንነነቶች ታፍኖ ተወሰደ

ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል  ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ የወሰዱት ሲሆን ለእስሩ ምንም አይነት ምክንያት ወይንም መጥሪያ እንዳልሰጡት ጋዜጣው ዘግቧል። አቶ ስንታየሁ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመበት ታውቋል።