ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ዶክተርን ኮሳዛና ድላሚኒ የተፈጸመው ጥቃት በፍጹም ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ፤ በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው
ዜጎች ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
“ምንም ዓይነት ችግር ቢጋረጥብንም፣ ሟቾቹ የሀገሬው ሰው ይሁኑ አልያም የውጪ ሀገር ዜጋ፤ በህዝብ ላይ የሚፈጸምን ጥቃት በምንም ዓይነት ምክንያት ማስተባበል አይቻልም” ብለዋል- ሊቀመንበሯ።
የደቡብ አፍሪካ መንግስትና የኩዋ ዙሉ አካባቢ አገልግሎት ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ በመግባት ተጠቂዎችን በመርዳትና ሌላ ጥቃት እንዳይፈጸም የፖሊስ ኃይል በማሰማራት እየወሰዱት ያለውን
እርምጃ ኮሚሽኑ አድንቋል።
የአፍሪካ ህብረት መስራች አባቶች የፊታችን ሜይ 25 እንደሚዘከሩ የጠቆሙት ኮሚሽነሯ፤ የህብረቱ አባቶች ሊዘከሩ በተቃረበበት ወቅት የዚህ ዓይነት ጥቃት መፈጸሙ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።
በደቡብ አፍሪካውያን ላይ የተጋረጡት የድህነትና የሥራ አጥነት ችግሮች በሁሉም ሀገሮች የተጋረጡ ችግሮች መሆናቸውን የጠቀሱት ኮሚጽነር ድላሚኒ፤ ሁላችንም አንድ ላይ ሆነን በመሥራት
ለወደፊት የተሻለች አፍሪካን መገንባት አለብን ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ አፍሪካውጥ ጥቃት ክፉኛ የተቆጡት የዚምባቡዌው መሪ ሮበርት ሙጋቤ ደቡብ አፍሪካውያንን ነቅፈዋል።
ሙጋቤ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት አነጋጋሪ አስተያዬት፦ «ትናንት ደቡብ አፍሪካኖች የሞተን የ”ነጭ” ሰው ሃውልት አፈረሱ፤ ግን አንድን በህይወቱ ያለን “ነጭ” በጥፊ እንኳን ለመምታት አልሞከሩም ነበር።
ዛሬ ግን “ጥቁር” ወንድማቸውን በቁሙ እያቃጠሉ ነው፤ የውጭ ዜጋ ስለሆነ ብቻ!! »በማለት ነው የተናገሩት።
በሌላ በኩል በደቡብ አፍሪካ በውጪ ሀገር ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት ተከትሎ ሞዛምቢክንና ደቡብ አፍሪካን የሚያገናኘው ድንበር ተዘጋ።
ኮሪደር ጋዜጣ እንደዘገበው ጥቃቱ ያስቆጣቸው ሞዛምቢካውያን በሀገራቸው ቆሞ የነበረን የደቡብ አፍሪካ ታርጋ ያለውን የጭነት መኪና በድንጋይ በመቀጥቀጥ ቁጣቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
ወደ 200 የሚሆኑ ሞዛምቢካውያን ከሬሳኖ ጋርሺያ ድንበር በምስራቅ በኩል አራት ኪሎ ሜትር አካባቢ የጭነት መኪናው በቆመበት ቦታ በመሰባሰብ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ አግደዋል።
እንደ ጋዘጣው ዘገባ በደቡብ አፍሪካ በውጪ ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ እንዲህ ያለ ነገር ሊያስከትል እንደሚችል የተጠበቀ ነው።
ከስዋኔ ሰሎሞን ማላንጉ እስከ ሞዛምቢኩ ማፑቶ ወደብ ድረስ ለተዘረጋው 570 ኪሎ ሜትር መንገድ ኃላፊነት “ትራክ”የተሰኘው ኩባንያ ተቃዋሚዎቹ ሞዛምቢካውያን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ
በድረ-ገጹ ላይ ማስጠንቀቂያ አስቀምጧል።
ከማፑቶ ወደ ኔልስፕሩት ሲጓዙ የነበሩ መንገደኞች -በሞዛምቢክ የተመዘገበ መኪና ስለያዙ ተቃዋሚዎቹ እንዲያልፉ እንደፈቀዱላቸው ለድረ-ገጹ ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና በለንደን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በ እንግሊዝ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ በመሰባሰብ በ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት በ አስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።
የወገኖቻቸውን ጥቃት እንደሰሙ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት በአስቸኳይ የተሰባሰቡት ሰልፈኞቹ፤ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮን በደቡብ አፍሪካ በውጪ ዜጎች ላይ በሙሉ የተፈጸመውን ጥቃት
በማውገዝ፤ የደቡብ አፍሪካ መንግስት የስደተኞችን ህይወት እንዲታደግና ዳግም የዚያ አይነት ድርጊት እንዳይፈጸም መንግስታዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።