ሚያዝያ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዛሬ ሚያዝያ 9/2007 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀን በሚከበረው ‹‹የመምህራን ቀን›› የኢህአዴግ አባል የሆኑ መምህራን ብቻ መሸለማቸውን ነገረ ኢትዮጵያ
በዝግጅቱላይ የነበሩ መምህራንን ዋቢ አድርጎ ዘገበ፡፡
በተማሪዎች ዘንድ ብቃት የላቸውም ተብለው ቅሬታ የሚነሳባቸው መምህራን የገዥው ፓርቲ አባል በመሆናቸው ብቻ ‹‹ምርጥ መምህራን›› ተብለው እንደተሸለሙ የገለጹት መምህራኑ ‹‹ከመቶው 90፣
80…. አግኝተዋል ተብለው ከመሸለማቸውውጭ መስፈርቱም ግልጽነት የጎደለውና ወገንተኛ እንደሆነ በግልጽ ተገንዝበናል›› ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በታህሳስ ወር 2007 ዓ.ም በፈጠራ ውጤታማ የሆኑትን መምህራን ሸልመው እንደነበር ያስታወሱት መምህራን
‹‹በአገር ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈጠራ ሙያቸው
የተሸለሙት መምህራን አሁን በከተማደረጃ ለተደረገው ሽልማት እንደማይበቁ ተደርጎ ከሽልማቱ መገለላቸው መምህራኑን አነጋግሯል›› ብለዋል፡፡
ዛሬ በተከበረው በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሸለሙት እንዳይካተቱ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያት የኢህአዴግ አባል ባለመሆናቸው እንደሆነ፣
በሌላ በኩል የኢህአዴግ አባል የሆኑትና በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም የተሸለሙትአሁንም መሸለማቸው የድርጅቱ አባል ያልሆኑትን መምህራን ሆን ተብሎ ለማግለል ያለመ ነው ብለዋል፡