መጋቢት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በመጪው ግንቦት ወር ምርጫ የምርጫ ካርድ ያልያዙ ሰዎች ስኳርና ዘይት እንደማያገኙ እንደተነገራቸው ለኢሳት ተናግረዋል።
አንዳንድ ቀበሌዎች የምርጫ ካርድ ዘይትና ስኳር ለመሸጥ የምርጫ ካርድ አብረው የሚጠይቁ ሲሆን፣ ካርድ ላልወሰዱት እንዲወስዱ እየጠየቁ ነው።
መራጮች የመምረጥም ሆነ ያለ መምረጥ መብት ቢኖራቸውም ፣ ገዢው ፓርቲ ከስኳርና ዘይት ጋር ማያያዙ ተገቢ አለመሆኑን ነዋሪዎች አክለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ኢህአዴግበ97 ምርጫ ከ193 በላይሰዎች መገደላቸውን አምኗል፡፡ የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነቸው አዲስ ራእይ መጽሄት በየካቲ- መጋቢት እትሟ ቀጣዩምርጫምከሰጋትነፃአይደለምብላለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ 25 ፓርቲዎች በተሳተፉበት የ1984 መለስተኛ እና አካባቢያዊ ምርጫ ከአሜሪካ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ተወክሎ የነበረውን ኤድመንድ ኬለር የተባለውን ጥቁር አሜሪካዊ ለኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር ወግነሃል
በሚል በ24 ሰአት አገር ለቆ እንዲወጣ እርምጃ እንደወሰደበት ያትታል፡፡ በሶስተኛው አገራዊ ምርጫ የ193 ወገኖች ህይዎት ለህልፈት ተደርጓል የሚለው አዲስ ራዕይ ፤በከተማ ደረጃለደረሰውውድቀት፤የወጣቱንተስፋመቁረጥ፤የተቃዋሚ ፓርቲዎችን
የምርጫስትራቴጅ – የአመፅሰልትናእናየቀለምአብዮትበምክንያትነት ጠቅሷል፡፡ ተፎካካሪእናተቃዋሚፓርቲዎችበአንደኛእናበሁለተኛው ምርጫዎች ከነባራቸው 12 ወንበሮች ፣ በ1997ዓም 30 በመቶመቀመጫ ለማግኘት መቻላቸውን
የሚያትተው መጽሄቱ፣ የአዲስአበባንወንበርከአንድበስተቀርሙሉ በሙሉ ማሸነፋቸውንም አትቷል፡፡
ከአፍሪካውያንበስተቀር ሌላ የውጭ አገር ታዛቢ አላስገባምየሚለውኢህአዴግ ፣ የውጭ ሃይሎች ስልጣንአስነጥቀውእስከመያዝአቅምእንዳላቸውያትታል፡፡
በአምስተኛውምርጫ አክራሪነት፤ፅንፈኝነት፤ተቃዋሚዎችበምርጫየሚወስዱትአቋም ያሰጋናል ያለው ኢህአዴግ፣ የውጭታዛቢዎችጉዳይበህግበመታገዱምክንያት የምንፈራውየውጭሃይሎችተፅኖአይኖርም ሲል ከውጭ ስጋት
ነጻ መሆኑን ገልጿል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የአውሮፓ ህብረት ምርጫውን የማይታዘበው ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት ምክንያት ነው ብለው ለፓርላማ መናገራቸው ይታወሳል።
የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ ከዚህ ቀደም ያቀረብኩት የምርጫ ትዝብት ሪፖርት ተቀባይነት ባለማግኘቱ ቀጣዩን ምርጫ መታዘቡ ትርጉም እንደሌለው፣ ከመንግስት በኩልም ምርጫውን እንዲታዘብ ጥሪ እንዳልቀረበለት ተናግሯል።
አዲስ ራእይ ከአፍሪካውያን በስተቀር የሌሎች አህጉሮች የምርጫ ታዛቢዎች እንዳያስታፉ ህግ መውጣቱን ቢናገርም ህጉ መቼና እንዴት እንደወጣ የሚታወቅ ነገር የለም።