የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢጋድ ሊቀመንበርነታቸው ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት የደቡብ ሱዳንን መንግስትና ተቃዋሚውን ሃይል ለማቀራረብ ለወራት ሲደከምበት የነበረው የሰላም ድርድር ያለውጤት ተበትኗል። ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ያለፉትን 4 ቀናት በአዲስ አበባ ያሳለፉ ቢሆንም፣ መሰረታዊ በሚባሉት የስልጣን ክፍፍል፣ ፌደራሊዝም እንዲሁም በሰራዊት ውህደትላይ መግባባት ሳይችሉ ቀርተዋልአቶ ሃይለማርያም ያለንን ሃይል ሁሉ ተጠቅመን የደቡብ ሱዳን መንግስት በሃምሌ ወር የሽግግር ጊዜ መንግስት እንዲመሰረት እናደርጋለን ብለዋል።
የጸጥታ ምክር ቤት ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ስምምነት ላይ የማይደርሱ ከሆነ ማእቀብ እንዲጣልባቸው ውሳኔ አሳልፏል። ይሁን እንጅ ውሳኔው እስካሁን ተግባራዊ አልሆነም።