የህወሃት ታጋዮች ቅሬታቸውን ገለጹ ።

የካቲት ፲ (አስር) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ  (ህወሃት) የትጥቅ ትግል የጀመረበት 40ኛ ኣመት በዓል በስኬት ላይ ብቻ የተመሠረተና ከበሮ ድለቃ የበዛበት የህወሃትን ጉድፎች የተደበቁበት ሆኖ እየተከበረ መሆኑ አሳዛኝ ነው ሲሉ የቀድሞ የድርጅቱታጋይገለጹ፡፡

ስማቸውእንዲገለጽያልፈለጉትየድርጅሩ የቀድሞታጋዮች ለኢሳት በላኩት መልእክትህወሃትየደርግአገዛዝበትጥቅትግል ለማሸነፍከሌሎችየትግልሃይሎችጋርበጣምራናበተናጠልሲታገልመቆየቱናአስከፊውንስርኣትመገርሰሱመልካም ነገር መሆኑ ባይካድም፣  ድርጅቱበሺየሚቆጠሩታጋዮቹን ለሞት ዳርጎ መንግስታዊስልጣን ከተቆናጠጠበሃላየታገለለትዓላማበመርሳትጥቂትሹማምንትራሳቸውንናቤተሰቦቻቸውንየሚያበለጽጉበት፣ቡድናዊ ወገንተኝነትበመመስረትብዙሃኑንያገለለስርዓትእንዲፈጠርአስተዋጽኦአድርጎአልብለዋል፡፡

ህወሃትመንግስታዊስልጣንላይበቆየባቸውባለፉት 23 ኣመታትዴሞክራሲ፣የህግየበላይነትእናየሰብዓዊመብት ጥበቃለማክበርናለማስከበርመታገሉንበመርሳትደጋግሞከሚረግመውየደርግስርዓትባልተናነሰአፋኝስርዓት እየገነባመምጣቱየፓርቲውንመክሸፍቁልጭአድርጎያሳያልሲሉ እነዚሁ ታጋዮች በመልክታቸው አስፍረዋል።

በትግልወቅትስንትናስንትጉዋዶቻችንንከአጠገባችንአጥተናልያሉትእኚሁየቀድሞታጋዮች፣ይህሁሉመስዋዕትነት የተከፈለውግንጥቂትየህወሃትሹማምንትንለማበልጸግሳይሆንበመላሀገሪቱሠላም፣ዴሞክራሲናእኩልነት እንዲሰፍንነበርብለዋል፡፡

በአሁኑወቅትኢትዮጽያውስጥሃሳብንበነጻመግለጽ፣ተደራጅቶየተቃውሞጠንካራእንቅስቃሴማድረግ፣የተቃውሞ ሰልፍማካሄድ፣ነጻየሲቪክማህበርማቋቋምበሸብርተኝነትጭምርእያስከሰሰ፣ዜጎችንምለእስርናለሞትናለስደት እየዳረገያለውበህወሃትጥቂትከፍተኛካድሬዎችአመራርሰጪነትመሆኑማንምአይዘነጋውምሲሉ አትተዋል።

በአሁኑወቅትየትግራይሕዝብየታገለለትንኣላማበራሱልጆችመነጠቁንያስታወሱትእኚሁታጋይየትግራይሕዝብና አመራሩበመለያየቱከፍተኛባለስለጣናትበመቀሌከተማየሰሩዋቸውንመኖሪያቤቶችሳይቀር «ሙስናሰፈር» ብሎ እስከመሰየምመድረሱሕዝቡለህወሃትያለውንትክክለኛአቋምያንጸባርቃልሲሉአክለዋል፡፡

የህወሃት 40ኛዓመትበዓልየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ምበትግራይለማክበርሽርጉድእየተባለሲሆን በተከታታይሰሞኑንየራያዩኒቨርሲቲየመሰረትድንጋይ፣የመቀሌታጁራወደብየባቡርግንባታየመሰረትድንጋይ መጣሉ፣የሞሃለስላሳመጠጥፋብሪካግንባታምረቃ፣የራያቢራፋብሪካግንባታምረቃናየመሳሰሉትበማከታተል የህዝብንድጋፍለመሳብህወሃትተግቶእየሰራሲሆንበዚህበምርጫወቅት፣በመንግስትመገናኛብዙሃንየሚደረገው የአንድፓርቲየተጋድሎፕሮፖጋንዳ፣በመንግስትወጪየሚደረገውጉሮወሸባዩሕገወጥመሆኑንእንኩዋንአልተረዱትም ሲሉአስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡

ህወሃት ለበአሉ ዝግጅት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያወጣ ሲሆን፣ ባላሃብቶች በግዳጅና በማስፈራሪያ እስካሁን ከ50 ሚሊዮን ያላነሰ ገንዘብ አዋጥተዋል።