በትጥቅ ትግል የሚያምኑ ሶስት የአፋር ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በስልጣን ላይ ያለውን የህወሃት /ኢህአዴግ መንግስት በሃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ የአፋር ድርጅቶች ማለትም አርዱፍ፣ ጋድሌና የአፍዴራ ታጋዮች የካቲት 8 ቀን 2007 ዓም የጋራ ግንባር ፈጥረዋል።

የአርዱፍ ሊቀመንበር አቶ  ኢብራሂም ሙሳ ለኢሳት እንደገለጹት ሶስቱም የአፋር ድርጅቶች በተናጠል ሆነው መዋጋታቸው ለስርአቱ እድሜ መርዘም አስተዋጽኦ በማድረጉ በቅድሚያ ድርጅቶቹ የጋራ ግንባር ፈጥረው በጋራ ለመዋጋት አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ በመድረሳቸው፣ በአንድ ወታደራዊ እዝ ስር ሆነው ለመታገል ወስነዋል።

አዲሱ ግንባር ከሌሎች የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር ለመታገል ፍላጎት  እንዳለውም አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።

ድርድሩ የተካሄደው በአፋር ህዝብ ፓርቲ በኩል መሆኑንም ለማወቅ ተችሎአል።

ከአቶ ኢብራሂም ሙሳ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ከዜናው በሁዋላ ይቀርባል።