የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተለያዩ አገሮች ተከበረ

የካቲት ፱ (ዘጠኝ) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-በኖርዌ የነበረውን ስነስርአት በተመለከተ ከአቶአበበ ደመቀ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል።

በአውስትራሊያሜልበርንከተማ  እሁድ  ፈብራሪ 15፣ 2015 ዓ .ምበደማቅሁኔታተከብሯል።

ፕሮግራሙ በህሊና ጸሎት ከተጀመረ በኋላ አቶ አንዳርጋቸውን የሚያስታውሱ በቪዲዮ የተቀነባበሩ ስነ ግጥሞች ፣መዝሙሮች እና  ዘጋቢ ፊልሞች ቀርበዋል።

የፕሮግራሙአስተባባሪዎች፦  <<የአቶ አንዳርጋቸውን 60ኛ አመት የልደት በአልየምና ከብረው፤  አቶ አንዳርጋቸው የከፈሉትን ዋጋ በመዘከር ፣እርሳቸው እየተሰዉለት ያለውን አላማ ለማስቀጠል እና ህዝቡም በከፍተኛ ሁኔታ ትግሉን እንዲቀላቀል ለማድረግ  በማሰብነው>> ብለዋል።

እንግሊዝ አቶአንዳርጋቸው  ስላሉበት ሁኔታ በቂ ትኩረት አለመስጠቷን የሚያሳስብ ደብዳቤ እና የአቶ አንዳርጋቸውን የጨለማ ቤት እስር የሚያሳይ የልደት ፖስትካርድ አንድ ላይ በማድረግ ለእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን “በሪጂስተርድ” ፖስታ መላኩን እና ደብዳቤው በግልባጭ በአውስትራሊያ የንግስት ኤልሳቤጥ ተወካይ ለሆኑት ለአገረገዥው ጴጥሮስ ዮሐንስ ኮስግሮቭ  እንዲደርስ መደረጉን  ገልጸዋል።

ፕሮግራሙ 60 ቁጥር ሻማን በመለኮስና ለልደቱ የተዘጋጀውን ዳቦ በመቁረስ  በውይይት እንዲቀጥል  የተደረገሲሆን ፤በስተመጨረሻ  “አቶ አንዳርጋቸው የጀመሩትን አላማ ለመፈጸም ትግሉን መቀላቀል አለብን”ብለው  የወሰኑ ኢትዮጵያውያን የድርጅት አባልነት ፎርም መሙላታቸውን ከአስተባባሪዎች መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ሃና ለገሰ ለኢሳት ገልጸዋል።

በስዊዘርላንድም እንዲሁ የአቶ አንዳርጋቸው 60ኛ አመት የልደት በአል ታከብሯል። አቶ አንዳርጋቸው እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ በስካይፕ ለተሰብሳቢው ንግግር አድርገዋል።

በእለቱ 10 አባላት ያሉት የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ መዋቀሩን የደረሰን ዜና ያመለክታል።