ለሳምንታት ክትትል ሲደረግባቸው የነበረው መምህር ጥጋቡ ሃብቴ ታፍነው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ

የካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ) የጎንደር ሰብሳቢና የመኢአድ መስራች የሆኑት መምህር ጥጋቡ ሃብቴ ለሳምንታት ማስፈራሪያ ሲደርሳቸውና ክትትል ሲደረግባቸው ከቆዩ በሁዋላ የካቲት 4/2007 ዓም ደህነቶች ሌሊት ወደ ቤታቸው በመግባት ፍተሻ ካካሄዱ በሁዋላ ወደ አልታወቀ ቦታ አፍነው ወስደዋቸዋል።

የቀድሞው የመኢአድ አዲስ አበባ ህዝብ ግንኑነት ሃለፊ አቶ አወቀ አባተ ለኢሳት እንደገለጸው ፣ መምህር ጥጋቡ የጎንደሩን ጽ/ቤት ለአዲሱ መኢአድ እንዲያስረክቡ ቢታዘዙም፣ አላስረክብም ብለው እንደነበርና ከራሳቸው ጽ/ቤት እንደሚታሰሩ ተነግሯቸው ነበር።

የመምህር ጥጋቡ ባለቤት ” ባለቤታቸው ታፍነው መወሰዳቸውን በመቃወም ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፣ “ለምርመራ ይፈለጋል” የሚል መልስ ከማግኘት ውጭ ሌላ የተነገራቸው አሳማኝ ምክንያት የለም።

አቶ አወቀ እንደገለጹት መምህር ጥጋቡ የታሰሩበትን ቦታ ለማወቅ ጥረት ቢደረግም እስካሁን አልተሳካም።

በሌላ በኩል ደግሞ የአንድነትፓርቲምክትልአፈጉባኤየነበሩትናበቅርቡየሰማያዊፓርቲንየተቀላቀሉትአቶጸጋዬአላምረውመሰደዳቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ከፀረ-ሽብርግብረኅይልእንዲታሰሩየማዘዣወረቀትመዉጣቱንተከትሎ  ለተወሰነቀናትአገርቤትራሳቸውንሰዉረውየቆዩትአቶጸጋዬ፣በአሁኑወቅትከኢትዮጵያዉጭመሆናቸውተረጋግጧል።

አቶሃብታሙአያሌውመታሰራቸውንተከትሎየመኢአድአመቻችኮሚቴሆነውየሰሩትአቶጸጋዬ፤በገሽውፓርቲ  ተጽእኖሳይሳካቢቀርም፤በመኢአድእናበአንድነትመካከል  ተጀምሮየነበረውየዉህደትሂደትእንዲሳካ  ከፍተኛአስተዋጽኦ ከተጫወቱትየአመራርአባላትመካከልአንዱእንደነበሩተመክቷል።

አቶጸጋዬ  በቅርቡበርካታየአንድነትአባላትንይዘው  ሰማያዊንከተቀላቀሉበኋላ  በገዝውፓርቲኢላማውስጥመግባታቸውንያመለከተውየነገረ-ኢትዮጵያዘገባ፤፣የቀረበባቸውክስም፦ “አንድነትፓርቲየገንዘብእርዳታከሽብርተኞች  እርዳታሲቀበልየቆየውበአቶጸጋዬአላምረውበኩልነበር”” የሚልነው።

ራዲዮፋናንጨምሮ  በገዝውፓርቲቁጥጥርስርያሉት  ቴሌቪዝንና  ራዲዮዎች፤በአንድነት  ፓርቲላይ  የስምማጥፋትዘመቻ  ከመክፈታቸውምበላይ፣ትእግስቱአወሉ የተባሉትን ሰውእየጋበዙ  – “ጸጋዬካልታወቁአካላትገንዘብይቀበልነበር” የሚልአሉባልታሲያሰራጩመቆየታቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።