የካቲት ፫(ሦስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-የከንባታ ጠንባሮ ህዝብ ባለፉት 23 አመታት የመሰረተ ልማት አገልግሎት አላገኘም በሚል ከሺ ያላነሱ ነዋሪዎች በተገኙበት በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል። የአካባቢው ተወላጆች በራሳቸው ተነሳሽነት ትምህርት ቤቶችን እየሰሩ ፣ የመብራት፣ የመንገዶችና የቴሌኮሚኒኬሽን ዝርጋታ ማካሄዳቸውን ገልጸው፣ መንግስት ምንም ድጋፍ ባለማድረጉ፣ ችግሩ የባሰባቸው ነዋሪዎች እየተሰደዱ መሆኑን ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ የደቡብ ክልል ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርገዋል። በሰልፉ ላይ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ሳይቀሩ መሳተፋቸው ታውቋል።