ታኀሳስ ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ለ3 ቀናት የሚቆይ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ስብሰባ እንዲካፈሉ ቢጠሩም፣ መምህራኑ በስብሰባው ላይ ከተገኙ በሁዋላ፣ በአንድ ድምጽ ስብሰባ ኣንሳተፍም በማለት ጥለው ወጥተዋል። መምህራኑ መንገድ የመሳሰሉ የመሰረተ-ልማቶች አልተሟሉም፣ ለመምህራን በቂ የሆነ ክፍያ አይሰጥም በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ የተጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ታጅቦ መበተኑንና የመምህራኑ ያለተጠበቀ እርምጃ የአካባቢውን ባለስልጣናት ማስደንገጡን መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል።