ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊደራል ፍ/ቤት ከወንጀል ነፃ ናቸው በሚል ያሰናበታቸወን ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ነፃ አይደሉም በሚል ባቀረበው አቤቱታ ጉዳያቸው በክልሉ ካቢኔ መታየት ጀምሯል፡፡
የክልሉ ካቢኔ ባደረገው ውይይት ለሁለት የተከፈለ ሲሆን አንደኛው ወገን እንፍታቸው ሲል ሌላው ወገን ደግሞ በምርጫው ላይ አሉታዊ ተጽኖ ስለሚያሳርፉ መፈታት የለባቸውም በሚል ሲከራከሩ ከቆዩ በሁዋላ ምርጫው ሳይጠናቀቅ መፈታት የለባቸውም የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል። ፍርድ ቤት ያስተላለፈው ውሳኔ በመስተዳድሩ ባለስልጣናት መቀልበሱን የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች።
የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቢ ህግ በ2007 በስድስት ወራት ብቻ በ231 ግለሰቦች ላይ ክስ የመሰረተ ሲሆን ማሸነፍ የቻለው ሁለት ብቻ ነወ፡፡