ታኀሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንዳንድ ተጓዞች ለኢሳት እንደገለጹት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ፍተሻ ጨምሯል። ከዲላ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ተሳፋሪ ለኢሳት እንደገለጸው ፖሊሶቹ ተሳፋሪውን ወዴት ነው የምትሄዱት? ለምንድነው የምትሄዱት በማለት ከመጠየቅ ጀምሮ የሰዎች ኪሶች በመግባት ፍተሻ ያደርጋሉ። በሽተኞችንና ህጻናትን የታቀፉ እናቶች ሳይቀሩ ፍተሻ በሚል ፖሊስ ጣቢያ ታጉረው መዋላቸውን አይን እማኞች ገልጸዋል። ድርጊቱን ሲታዘብ የቆየ አንድ መንገደኛ ዛሬ በፈታሾችና በተሳፋሪዎች መካከል የነበረውን እሰጥ አገባ ቀርጾ በላከው ቪዲዮ ላይ ህዝቡ በፍተሻው እየተማረረ መሆኑንና ፍተሻው መቀጠሉን የሚያረጋግጥ ነው