በጋምቤላ 2 የምክር ቤት አባላት አዲስ አበባ ላይ ታሰሩ

ታኀሳስ (አንድ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት  አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በካውች ማሞና ኦብዱል ኦቻር የሚባሉትን ባለስልጣኖች አውርዷቸዋል። ግለሰቦቹ ያለመከሰስ መብታችን የተነሳው በህገወጥ መንገድ ነው በማለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለማግኘት ሙከራ ቢያደርጉም፣ ደህንነቶች ይዘው አስረዋቸዋል። ባለስልጣኖቹ ከውጭ ሃይሎች ጋር ትገናኛላችሁ በሚል መከሰሳቸውን የአኝዋ ሰርቫይቫል ዋና ሃላፊ አቶ ኒካው ኦቻላ ለኢሳት ገልጸዋል