በበለሳ የጸጥታ ሰራተኞች እርስ በርስ ተታኩሰው ተጋደሉ

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ የጸጥታ አስተዳደር ሰራተኞች እርስ በርስ ሲገማገሙ ከቆዩ በሁዋላ ፖሊሶቹ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊውንና አቶ ባዩ ማሩንና ሌላ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊውን በጥይት ደብድበው ገለዋል። አቶ አባይ ማሩ በጃናሞራ ወረዳ መካነ ብርሃን ከተማ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህዳር 3 ቀን ተቀብረዋል። በተራ ፖሊስ አባላት የተወሰደው እርምጃ አመራሩን ድንጋጤ ውስጥ ከቷል።

ከግምገማ ጋር በተያያዘ የጸጥታ ሰራተኞች እርስ በርስ ሲገዳደሉ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው። ባለፈው ወር መግቢያ ላይ በላሊበላ አንድ ተገምጋሚ ፖሊስ ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ 2 ፖሊሶችን አቁስሎአል።