ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ አገሪቱ ከግል የገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋን ተከትሎ የኢትዮጵያን ብድር በበላይነት በሚያስተባብረው በጀርመን ትልቁ ባንክ አማካኝነት በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ተብሎአል።
ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ ገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋ ብዙ ኢኮኖሚስቶችን እያነጋገረ ነው። ጠ/ሚኒስትሩ ከጀርመን ቻንስለር አንግላ መርክል ጋር እንደሚነጋገሩም ታውቋል። አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ማዳበሪያ ከሚያቀርብ አራ ከተባለ የማዳባሪያ ድርጅት የግብርና ምርትን ለመጨመር ባሳዩት ጥረት
በሚል ሰበብ 200 ሺ ዶላር እንዲሸለሙ ተደርጓል። በተመሳሳይም ኢትዮጵያ ከጀርመን ባንክ በዋናነት ብድር ለመውሰድ መስማማቱዋ ጀርመን ለኢትዮጵያ መሪዎች የደመቀ አቀባባል ለማድረግ መወሰኑዋን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።
የአቶ ሃይለማርያምን በጀርመን በርሊን መገኘትን በመቃወም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።