ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰማያዊ ብርሃን ቤተክርስቲያን በመሄድ ማፍረሳቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አንድ ፓስተር እስከባለቤታቸውና ሌላ አገልጋይ ታስረዋል። የሃረር አብያተ ቤተከርስቲያናት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አምደማርያም ታስረው ሲፈቱ ሌላው የቤተክርስቲያኑዋ ፓስተር አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያኗ በአገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግባ የምትንቀሳቀስ መሆኗ ታውቋል።
የክልሉ አፍራሽ ግብረሃይል አባላት 30 በሚሆኑ ታጣቂዎች ታጅበው በመምጣት ቤተክርስቲያኑዋን አፍረርሰዋል። በክልሉ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ ለኢሳት ተናግረዋል።