ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን አመራሮች ሰሞኑን በዞኑ ባካሄዱት የወጣቶችና ሴቶች ጉባኤ ላይ ፣ የአካባቢው ወጣቶች የጸረ ሰላም ሃይሎች መሳሪያ ከመሆን እን ዲቆጠቡ ጠይቀዋል።
ወጣቶቹ በግፍ የታሰሩ የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አንጋው ተገኝ፣ አባይ ዘውዱና ሌሎችም አባላት ታፍነው መወሰዳቸውን ተቃውመዋል። በተለይ የጋብላ እና የዘመነ መሬቅ ወጣቶች እውን ዲሞክራሲ የሚባለው በዚህ አገር አለ ወይ በማለት የጠየቁ ሲሆን፣ የመንግስት በደሎች ያሉዋቸውን ዘርዝረው አቅርበዋል።
ሁሌ እንሰበሰባለን ጠብ የሚል ግን የለም ያሉት ወጣቶች፣ ስራ አጥነት በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱንም ገልጸዋል። በአካባቢው ያለው የመሬት ስሪት ሲሰራ ባለሃብቱን እንጅ ድሃውን ግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም ያሉት ወጣቶች፣ ይህን ተከትሎም ድሃው ህዝብ ለችግር ተዳርጓል ብለዋል።
በአካባቢው ከፍተኛ እውቅና የነበራቸው አንድነት አመራሮች መታሰር አሁንም ድረስ ከፍተኛ የህዝብ ቅሬታ እንደፈጠረ ነው።