ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ብሌስ ካምፓወሬን መንግስት በመገልበጥ ጊዜያዊ መሪ መሆናቸውን ካስታወቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን ለሲቪል አስተዳደር ያስረከቡት ሌ/ኮሎኔል አይዛክ ሲዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ጊዜያዊው ፕሬዚዳንት ሚኬል ካፋንዶ ኮሌኔሉን ጠ/ሚኒስትር አድርገው የሾሙት በስልጣን ጉዳይ ሲደረግ የነበረውን ድርድር ተከትሎ ነው።
ሁለቱም መሪዎች አገሪቱን ለአንድ አመት ያክል ካስተዳደሩ በሁዋላ ምርጫ ይካሄዳል። ፕሬዚዳንቱ በምርጫው እንደማይወዳደሩ ህጉ ይከለክላቸዋል። ጠ/ሚኒስትሩም በመጪው ምርጫ ይወዳደሩ አይወዳደሩ የሚታወቅ ነገር የለም።