ኀዳር ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ክልል የአስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ እንደተናገሩት በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ፤ ሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ስራ አጥ ወጣቶች በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እየተቀላቀሉ ነው።
የወረዳው ወጣቶችን ያወያዩት ሃላፊው ወጣት አርሶ አደሩ ተምሮ ስራ ካላገኘ ፤ ወይ የሚያርሰው መሬት ከሌለው ከትግል ውጭ ሌላ ምን መፍትሄ አለው ሲሉ ጥያቄ አንስተው ብቸኛው መፍትሄ ስራ አጥነትን መቅረፍ መሆኑን አመልክተዋል፡፡