ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ በመሰረተባቸው አቶ ዘላለም ወርቅነህ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሽዋስ አሰፋና በሌሎች 5 ተካሳሾች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ አራዘመ።
ፍርድ ቤቱ የሁሉም ጠበቆች ተዘጋጅተው ባለመቅረባቸው ውሳኔውን ለህዳር 2 ፣ 2007 ማራዘሙን አስታውቋል። እስረኞቹ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለወራት በእስር እየተሰቃዩ ሲሆን፣ በርካታ አለማቀፍ ድርጅቶች ክሱን ፖለቲካዊ ነው ይሉታል።
በሽብርተኝነት የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት እንደማይሰጠው የህግ ባለሙያዎች ይገልጻሉ።