ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ16 የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተይዘው በነበሩት ተማሪዎች ላይ ከ1 እስከ 5 በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በሌላ ዜና ደግሞ በአዳማ ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ተጎዱ።

የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት  ከከተማ አስተዳደሩ ቤት አፍራሽ ግብረ ሀይል  ህገወጥ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ወደ ስፍራው ቢንቀሳቀስም ወደ 1 ሺ የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ መጡበት ተመልሰዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ፖሊሶች በህክምና ላይ መሆናቸው ታውቋል።