ጥቅምት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ በጨርቆስ አካባቢ አንድ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሎ መገኘቱን እና ሌሊት ላይ በቦሌ አካባቢ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን የሚያስተጋቡ ወረቀቶች በየግድግዳውና የኤሌክትሪክ ፖሉ ላይ ተለጥፈው መገኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ውጥረት መንገሱን ነገረ ኢትዮጵያ በዘገባው አመልክቷል።
‹‹አንድ የጨርቆስ አካባቢ ነዋሪ ተገድሎ መገኘቱን ተከትሎ ‹የጨርቆስ ወጣቶች› ተሰባስበው ይህን ድርጊት ይፈጽሙ ይሆናል ብለው በገመቱት ላይ ቁጣቸውን” መግለጻቸውን የዘገበው ነገረ ኢትዮጵያ፣ እስካሁንም ውጥረቱ እንዳለ ገልጿል። ነዋረዎች‹‹እያንዳንዱ ሰው የሚወጣ የሚገባበት ሰዓት መመዝገብ ይጀመራል ተብለናል›› ብለው መግለጻቸውን ጋዜጣው አክሎ ገልጿል።