ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአሚባራ በአፋርና በኢሳ መካከል የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው ገድለው ሌላ የአፋር ተወላጅን ደግሞ አቁስለዋል። በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ከትናንት ጀምሮ ገዋኔና ቡድመዳ ወረዳዎች በጎርፍ መጥለቅለቃቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም በማለት ወቅሰዋል። በአዋሽ ቀበና ላይ የሚካሄደው የስኳር ፕሮጀክት እንዲሁም የመተሃራ የበሰቃ ውሃ ለአዋሽ ውሃ መሙላት መንስኤ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በዚህም የተነሳ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ ነው ብለዋል።