ጥረት ኮርፖሬት ከ 225 ሚልዩን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው ታወቀ

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ንብረት በሆነው ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ የሚገኙት ጣና ሞባይል ና ዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅቶች በያዝነው አመት ከ225 ሚልዩን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው

በ2007 ዓም መግቢያ ላይ በተደረገው የድርጅቱ ግምገማ ላይ ተገልጧል።

አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መሳደባቸውን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችን ለማሳመን የተደረጉ ስብሰባዎች ና የተሃድሶ መድረኮች ድርጅቱን ከፍተኛ ወጪ እንዳስወጡት በግምገማው ወቅት ተወስቷል።

አንድነት ፓርቲ ብአዴን ይቅርታ የማይጠይቅ ከሆነ በባህርዳር ከተማ በድጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ፣ አቶ አለምነውንም ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው መግለጹ ይታወሳል። ድርጅቱ በባህርዳር ካካሄደው ደማቅ የተቃውሞ

ሰልፍ በሁዋላ ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ እንቅስቃሴ ሲያደርግ አልታየም። የአቶ አለምነው ቤትና ልጆች አሁንም ድረስ በልዩ ሁኔታ እየተጠበቁ ሲሆን፣ አቶ አለምነውም ሆነ ብአዴን እስካሁን በይፋ ህዝቡን ይቅርታ አልጠየቁም።