መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመራው ስብሰባ ላይ ዳኞች የስርአቲ ደጋፊ እንዲሆኑ እየተገደዱ ባለበት ሁኔታ እንዴት ነጻ ዳኝነት ሊሰጥ ይችላል በማለት ጠይቀዋል።
የድርጅት አባላት ያልሆኑ ዳኞችም ስራቸውን ለመስራት እየተቸገሩ መምጣታቸውን መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።
ይሄው በመላው አገሪቱ በሚደረገው የፖለቲካ ስልጠና የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አባላት ሳይቀሩ በስርአቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ እየገለጹ ይገኛሉ።