አቶ ኦኬሎ አኳይ ተደበደቡ

መስከረም (አሥራ ሦስ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በእስር ቤት ውስጥ ከሌላ እስረኛ ጋር ተጋጭተዋል በሚል ሰበብ ከፍተኛ ድብደባ

ከደረሰባቸው በሁዋላ ጸሃይ ላይ ለረጅም ሰአት እንዲቀመጡ ተደርገዋል።

አቶ ኦኬሎ ድብደባው የተፈጸመባቸው ቂልንጦ እየተባለ በሚጠራው  እስር ቤት ውስጥ ሲሆን፣ በእስር ቤት ሃላፊዎች መረጃ እንዲያቀርብ ተብሎ ሳይመደብ እንዳልቀረ ከሚነገርለት እስረኛ ጋር መጠነኛ ግጭት ውስጥ ከገቡ በሁዋላ፣

እስረኛው ሄዶ ካመለከተ በሁዋላ ነው። አቶ አኮሎ መንግስትን በሃይል ለመገልበጥ በሚል ወንጀል መከሰሳቸው ይታወቃል።