መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ17 የጅቡቲ፣ ህንድ፣ የተባበሩት
አረብ ኢምሬትስ፣ ሲሪላንካና እና አሸራፍ አወል አብዲ በሚባል ኢትዮጵያዊ ላይ በመሰረተው ክስ፣ ግለሰቦቹ ለኢትዮጵያውያን በተፈቀደው የንግድ ስራ ህገወጥ በሆነ መንገድ በመነገድ መንግስት ማግኘት
የነበረበትን 700 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ እንዲያጣ አድርገዋል ብሎአል።
በክሱ ዱባይ ኦቶ ጋላሪ ኤል ኤል ሲ እና ወርልድ ኢንተርናሽናል ፍሪዞን ኩባንያ ሰራተኞች የሆኑት 2 የሲሪላንካ
ዜግነት ያላቸው ሰዎች፣ አካፔ ኢምፔክስ በሚል ስም በአቶ አሸሪፍ አወልና በወ/ሮ ሲና ሙሃመድ ባለቤትነት በተቋቋመው ኩባንያ ስም የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ሲሸጡ እንደነበር ተመልክቷል።
አቶ አሸሪፍና ወ/ሮ ሲና ዱባይ ከሚገኙት ኩባንያዎች ጋር በመመሳጠር ካገኙት ከ520 ሚሊዮን ብር በላይ ከሆነ
ገንዘብ ውስጥ 104 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በኢትዮጵያ ባንኮች ማስቀመጣቸውም በክስ ቻርጁ ላይ ሰፍሯል።
ከ 1 አመት በፊት ሁለቱ ተጠርጠራዎች መያዛቸውን ተከትሎ ኢሳት ዱባይ የሚገኘውን የአውቶ ጋላሪ ሃላፊን ባነጋገረበት ወቅት፣ሃላፊውበኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞቹ ስለመያዛቸው ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ
ገልጾ ነበር።