የወረዳው ገንዘብ ያዥ ገንዘብ ይዘው ተሰወሩ

ጳጉሜን ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃድያ ዞን ሚሻ ወረዳ ሞርሲጦ ከተማ ነዋሪ የሆኑት

አቶ አባይነህ ቁጥሩበውል ያልተወቀ ከፍተኛ ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸውን የኢሳት አካባቢው ምንጮች

ተናግረዋል።

አቶ አባይነህ ገንዘቡን ይዘው እንደጠፉ ስልክ ሲደወልላቸው ” የድርሻየን ወስጃለሁ” የሚል መልስ

መስጠታቸውንና ስልካቸውን ማጥፋታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

ለወረዳው ስራ ማስኪያጃ የሚውለውን ገንዘብ ይዘው በመጥፋታቸው የወረዳውን ስራ ለማካሄድ

ችግር መፍጠሩን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።

ግለሰቡን ለመያዝ ፖሊስ ክትትል እያደረገ ቢሆንም እስካሁን አልተሳካለትም።