ነሃሴ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላው አውሮፓ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ይህ የተቃውሞ ሰልፍ እጅግ ደማቅ መሆኑን
ወንድማገኝ ጋሹ በስልክ ገልጿል።
የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ተላልፈው ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ሰብአዊ መብታቸውን በመግፈፍ
በኢትዮጵያውያን እንዳይጎበኙ ከልክሏል።
አብዛኛውን ስራቸውን እንዳጠናቀቁ በተደጋጋሚ ሲናገሩ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ወደተለያዩ ቦታዎች በሌሊት እየተዘዋወሩ ምርምራ እየተደረገባቸው
መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን ለመያዝ ከፍተኛ ገንዘብ ለየመን የጸጥታ ሃይሎች መክፈሉን
መዘገባችን ይታወሳል።