ነሃሴ ፳፱(ሃያዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ አባላት ስብሰባ ፣ አባላቱ ዛሬም
በርካታ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ መዋላቸውን ከውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአባላቱ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፡- ” የኢትዮጵና የኤርትራ ህዝቦች የማይነጣጠሉ የአንድ ሃገር ዜጎች ሆነው ሳለ በመሪዎች አለመግባባትና
ሽኩቻ በመለያየታቸው እስከዛሬ ድረስ እየተላቀሱ ይገኛሉ፤ ይህም የሆነው በኢህአዴግም አስተዋፆ ጭምር ነው፤ አሁንም ቢሆን ከኛ ጋር መስማማት ከፈለጉ
በራችን ክፍት ነው የምትሉት ከልባችሁ ነወይ?” የሚለው ጥያቄ ሰፊ ሰአት ወስዶ ማከራከሩ ታውቋል።
በሃይማት አክራሪነት ጉዳይ ለተነሱት ጥያቄዎች ደግሞ ” ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰልፍ በጠራበት ጊዜ ሰልፈኛው መስኪድ አካባቢ ሲደርስ ሙሉ ለሙሉ
ለጸሎት ወደ መስኪድ እንደገባ አረጋግጠናል፤ ስለሆነም
” መንግስት ሁሉንም ሚዲያዎች እንደጥፋተኛ ቆጥሮ ጋዜጦችና መጽሔቶችን እንዳለ ከገበያ ማስወጣቱ እኛ አባሎቹ የኢህአዴግን ክፍተት የምናውቅበት መንገድ
ተዘግቷል፤ ኢህአዴግ ለስራ አጥ ዜጎች የስራ ዕድል እፈጥራለሁ እያለ በአንፃሩ ግን የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ዜጎች በአባልነት ላይ የተመረኮዘ ለምን ይሆናል?
በታችኛው ህብረተሰብ አካባቢ በብልሹ አሰራር ውስጥ ገብተው ከፍተኛ ሙስና የሰሩና በህዝቡ የተገለሉ ሰዎች ተሸፍነው ወደ ላይ ሲወጡ ሹመት ይደረብላቸዋል
ይህ ተገቢ ነወይ?” የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።
የአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ጉዳይም ሰፊ አጀንዳ የነበረ ሲሆን፣ ኢህአዴግ በሰላማዊና ጠንካራ ተቃዋሚዎች ላይ የያዘው አቋምም ትችት አዘል ጥያቄ አስነስቶበታል።
የዛሬውን የፕላዝማ ውይይት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው መርተውታል።
ትናንት ከሰአት በሁዋላ በነበረው የውይይት ጊዜ ደግሞ ” ኢህአዴግለሃገሪቱስጋትብሎከለያቸውየፖለቲካጉዳዮችውስጥዋነኛያላቸውየሃይማኖትአክራሪነት ወይም
ጽንፈኝነትእናየመልካምአስተዳደርእጦትቢሆኑም፣ የኑሮውድነቱ በስጋትነት ሊካተት ይገባል” የሚል አስተያየት ቀርቧል።
የደመወዝጭማሪውአርኪአለመሆኑናእንዳውምየበለጠህዝቡንናየመንግስትሰራተኛውንለችግርመዳረጉም በአባላቱ ተነስቷል።
ሰልጣኞቹንበሚሰለጥኑበትቦታጥያቄዎችሲነሱእዚያውበህዋሳቸው በሰልጣኞቹእንዲመለስበማሰብበህዋስ ማደራጀት መጀመሩን፣ ሰልጣኞቹየመድረኩንየፕሮፓጋን
ዳገለፃብዙትኩረትሳይሰጡየጥያቄናመልስክፍለጊዜሲደርስ ግን በንቃትጥያቄየሚያነሱ ሲሆን፣ አንዳንዳ ጥያቄዎችንከውይይሩጋርግንኙነትየላቸውም ወይም
ጥያቄውንወደኋላላይማንሳትትችላላችሁበሚል እንደሚታለፉ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ የግንቦት 7 ድርጅትአጀንዳየነበረሲሆንበአንዳንድአባላትዘንድግንቦት 7 ከውጭመንግስታትጋርበማበርበሀገርአብዮትእንዲነሳ
እየሰራነውሲሉሌሎችአባላትደግሞግንቦት 7 አሸባሪከተባለለምንየአሜሪካመንግስትአሳልፎአይሰጥም? እናንተእንደምትሉትአሸባሪቢሆንኖሮያስሩዋቸውነበር
ብለውተከራክረዋል፡፡አወያዮቹምከአሸባሪዎችጋርመገናኘትየለባችሁም፣በሀገርየሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎችአብረውእየሰሩእንደሆነለአባላቱየገለጹሲሆንንክኪ
እንዳይኖራችሁ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
በኢህአዴግ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው ግምገማ መነሻ፣ በቅርቡ ኢህአዴግ መዳከሙን የተመለከተ ግምገማ ከተደረሰ በሁዋላ ነው። ይህን ተከትሎ ለዩኒቨርስቲ
ተማሪዎች፣ ፖሊሶች፣ የህግ ባለሙያዎች በመንግስት ፖሊሲ ዙሪያ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል። በስልጠናው ላይ የተነሱትን ጥያቄዎች የኢህአዴግ አባላት እንዲመክቷቸው
በሚል እየተሰጠ ያለው ስልጠና ያልተጠበቁ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ፣ ከፍተኛ አመራሮችን ሳይቀር በእጅጉ ማስገረሙን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
“እዚህ የምናደርገው ስብሰባ በኢሳት ይዘገባል ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ? “በሚል አመራሩ እየተነጋገረበት መሆኑንም ታውቋል።
ብአዴንም መረጃዎች እየወጡ ተቸግረናል በሚል ትናንት በጀመረው ግምገማ ማንም ሰው ሞባይል ስልኮችን ይዞ እንዳይገባ ከልክሏል።