ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በአዲስ አበባ የሚገኙ መላ አባላቱን ለስልጠና ምቹ የሆኑ አዳራሾች ባሉዋቸው ትምህርት
ቤቶች እና የመንግስት ተቋማት ከትናንት ጀምሮ በፕላዝማ የታጀበ ስልጠና እየሰጠ ነው።
ስልጠናው በመላው አገሪቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያነሱዋቸው አፍራሽ የተባሉ ጥያቄዎች እና አመለካከቶች ወደ ህዝቡ ወርደው አደጋ ከመፍጠራቸው
በፊት የኢህአዴግ አባላት እንዴት እንደሚከላከሉዋቸው ስልጠና ለመስጠት ያለመ ቢሆንም፣ የድርጅቱ አባላት ግን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያነሱዋቸውን
ጥያቄዎች ደግመው እስከመጠየቅ በመድረሳቸው የድርጀቱ አመራሮች አባላት ያልሆኑ ሰዎች በስልጠናው ላይ ተገኝተዋልና እናጣራለን ብለው እስከመናገር
መድረሳቸውን በስልጠናው ላይ የሚሳተፉ አባላት ለኢሳት ገልጸዋል።
የመጀመሪያው ቀን ስልጠና የተሰጠው በኢህአዴግ የጽ/ቤት ሃላፊና በከንቲባው ልዩ አማካሪ በሆኑት በአቶ ተወልዴ ወ/ጻድቅ ሲሆን፣ ከተለያዩ የስልጠና
ቦታዎች የተነሱትን ጥያቄዎች በማንሳት መልስ ለመስጠት ሞክረዋል። በአባላቱ ዘንድ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል፣ ስለድሮ ታሪኮች መጥፎ መጥፎንውን
ብቻ ለምን ትነግሩናላችሁ? ውይይቱ ስለኢህአዴግ ጥንካሬና ድክመት ብቻ ቢሆን እንመርጣለን፣ ሚኒሊክ አገርን አንድ ያደረገ የመጀመሪያው መሪ ሆኖ ሳለ
ለምን ሁሌ በመጥፎ ይነሳል፣ አማራንና ኦሮሞን ለማጣላት ሆን ብላችሁ ታሪክ እያጣመማችሁ ነው፣ እናንተ ሳትማሩ እኛን የማሰልጠን ብቃት አላችሁ ወይ፣
ኤርትራን ያስገነጠላችሁት እናንተ እንጅ ሚኒሊክ አይደለም፣ ደርግ ኢትዮጵያ ትቅደም ይል ነበር እናንተ ደግሞ ዘር ይቅደም ትላላችሁ፣ አገሪቱን ከፋፍላችሁ
ለምን የቀድሞ ስርዓት ከፋፈለው ትላላችሁ፣ ታሪክን እኛ እናንብብ እንጅ እናንተ አታስተምሩን፣ የአንድ ዘር የበላይነት ነግሷል፣ የአሰብን ወደብ እንድናጣ
አድርጋችሁዋል፣ አማራን ተሳድባችሁዋል፣ የሚሉትና ሌሎችም ይገኙበታል።
አሰልጣኙ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ይህን አልተናገረም፣ ይህ አስተሳሰብና ጥያቄ በእኛ ውስጥ የለም፣ በየመጽሄቶችና ጋዜጦች ላይ የተለያዩ ሃይሎች የሚያቀርቡት
ውንጀላ ነው የሚል መልስ ከመስጠትና የምትጠይቁት ጥያቄ ከአንድ አባል አይጠበቅም በማለት ከመናገር ውጭ ለተነሱት ጥያቄዎች የቀጥታ መልስ
አለመስጠታቸውን አባላቱ ተናግረዋል። አባል ያለሆኑ ሰዎች በስልጠናው ላይ ተገኝተው ይሆናል በሚል ማጣራሪያ እንደሚደረግም አሰልጣኙ ገልጸዋል።
ስልጠናውንበቀጣይነትየተለያዩየፖለቲካአመራሮችበፕላዝማውፕሮግራም እየተቀያየሩእንደሚሰጡምታውቋል፡፡ስልጠናውደረቅናአሰልቺመሆኑ፤አስፈቅዶ
መውጣትናመግባትበላመቻሉእንዲሁምጥብቅቁጥጥርእየተደረገከመሆኑየተነሳብዙዎቹሰልጣኖች
እንቅልፍማንቀላፋት፣ማስቲካማኘክ፣የጆሮማዳማጫበመጠቀምሙዚቃማዳመጥ፣ፌስቡክመጠቀምእናጌምመጫዎትላይትኩረትማድረጋቸውንናቀን
ለማስቆጠርያክልመገኘታቸውንሰልጣኖች ይናገራሉ።
ዛሬ ከሰአት በሁዋላ በነበረው ውይይት ደግሞኢህአዴግኤርትራንበጠላትነትፈርጆሳለየኤርትራተወላጆችንናሌሎችየኤርትራተቃዋሚሃይሎችንይንከባከባል፤
ይህምንማለትነው? የሚልጥያቄተነስቶነበር።
መድረኩለስልጠናብቻሳይሆንየአባሎቹንወቅታዊየፖለቲካአመለካከትጭምርለመገንዘብ እና በድርጅቱ ውስጥ የሚታየውን ውጥረት ለማስተንፈስያሰበ
ይመስላልሲሉ አባላቱ አስተያየታቸውን ተናግረዋል። ኢህአዴግ በአዲስ አበባ 144 ሺ አባላት እንዳሉት ይናገራል።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በደረሰበት ድክመት አሰቸኳይ የክልሉን አመራር አባላት በባህርዳር ጠርቶ ለአምስት ቀናት የሚቆይ
ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው፡፡ በስብሰባውከ200 በላይየወረዳአመራሮች እየተሳተፉ ነው ፡፡ ድክመቶቻችንንበማራምኢህአዴግንእንዴትእናስቀጥል በሚል መሪ ቃል
የሚካሄደው ግምገማ ድርጅቱ ያገጠመውን የፖለቲካ ችግር ይግመግማል። የብአዴን ልቀመንብር ድርጅቱ ጠንካራ ግምገማ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
የኢህአዴግ ም/ቤት በቅርቡ ባካሄደው ጉበኤ ኢህአዴግ ተዳክሞል የሚል ውሳኔ ላይ በመድረሱ በደቡብ ክልል አዋሳም ተመሳሳይ ውይይት እየተካሄድ ነው ።
በሌላ ዜና ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ ባለው የፖለቲካ ስልጠና ተማሪዎች የመንግስትን ፖሊሶች ነቅፈዋል። ተማሪዎች የጠ/ሚኒስትሩ የስልጣን ጊዜ
እንዲገደብ፣ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ከአንድ ብሄር የተውጣጡና እስካሁን ስልጣናቸውን አለመልቀቃቸውን፣ የስልጣን ክፍፍሉ በአንድ ብሄር ብቻ የተያዘ መሆኑ፣
የሃይማኖት ነጻነት አለመኖሩ፣ የሃይማኖት መሪዎች የመንግስትን ፍላጎት እንዲያሟሉ መገደዳቸው፣ ስብሰባውን የሚያወያዩት የአንድ ብሄር አባላት ብቻ መሆናቸው
እንዲሁም በምርጫ 97 የተገደሉት ፍትህ አለማግኘታቸውን አንስተዋል።