የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አርባምንጭ መግባታቸውን ተከትሎ ወጣቶች እየታፈሱ ነው

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊታችን ቅዳሜ የሚከበረውን የአርባምንጭ የ50ኛ አመት የምስረታ በአልን የማጠቃለያ ዝግጅት

ለመካፈል ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በከተማዋ ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ

ወጣቶች እየታደኑ ነው።

ዘጋቢያችን እንደገለጸው፣ ከ3 ቀናት በፊት እናቶች በየቀበሌው እየተጠሩ ልጆቻቸውን እንዲሰበስቡ ተነግሮአቸው ነበር። ማንኛውም ወጣት በምሽት ከተማ

ውስጥ መዘዋወር፣ ሰብሰብ ብሎ መቆም እንዳይችል እየተደረገ ነው። አርባምንጭ ካለፈው ሁለት ወራት ጀምሮ የ50ኛ አመት የምስረታ በአሉዋን በማክበር

ላይ ትገኛለች።