ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ያለፈቃዳቸው እንዲላኩ የተደረጉት የቀድሞው የጋምቤላ
መሪ አቶ ኦኬሎ አኳይ እና ሌሎች ስድስት ተከሳሾች መንግስት ያቀረበባቸውን የሽብርተኝነት ክስ በማስተባባል የመቃወሚያ መልስ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ
መቃወሚያቸውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የክስ መቃወሚያውን ወድቅ ማድረጉን ተከትሎ የጥፋተኝነት ቃላቸውን እንዲሰጡ የታዘዙት እስረኞቹ፣
አቃቢ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ አለመፈጸማቸውን እና ንጹሃን መሆናቸውን አስረድተዋል።
እስረኞቹ በእስር ቤት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል። ፍርድ ቤቱ የእስረኞችን አቤቱታ ሳይቀበል፣ የምስክር ማሰማት ሂደቱን በመጪው
ጥቅምት ወር እንደሚጀምር አስታውቋል። አቶ አኬሎ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው ሲሆን ለስራ ወደ ደቡብ ሱዳን በተጓዙበት ወቅት ታፍነው መወሰደቻው ይታወቃል።
በጋምቤላ የሚታየው አለመረጋጋት አሁንም እንደቀጠለ ነው።