ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ
የስኳር፣ የቡናና ዱቄት እጥረት ተፈጥሯል። በዱቄት እጥረት የተነሳ በተለይ በአማራ ክልል ሰዎች ዳቦ ለማግኘት ራጃጅም ሰልፎችን
ተሰልፈው ወረፋ ለመተበቅ ተገደዋል። ቡና የመጨረሻ ደረጃ የሚባለው በኪሎ እስከ 100 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ ሁለተኛና አንደኛ
ደረጃ የሚባሉትን የቡና አይነቶች ፈልጎ ማግኘት አስቸጋሪ ሆናል ብለዋል። የስኳር እጥረቱም ካለፈው ወር ጀምሮ የተባባሰ ሲሆን፣
ለወትሮው በድጎማ ሲሸጥ የነበረው ፓልም የምግብ ዘይትም ከገበያ ጠፍቷል። መንግስት ካለፉት 3 አመታት ጀምሮ ስኳር እና ዘይት
በማከፈፋል ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።