ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፈቃዱ ሃይሌን ጠቅሶ እንደዘገበው
ከባቡር ፕሮጀክቱ ጋር የተያያዙትን መንገዶች ከመምራት ጋር የተያያዘ ችግር አለ። ዋና ስራ አስኪያጁ ያለምንም ዝግጅትና እውቀት የአስፋልት መንገድ
ይቆራጣሉ፣ በቅንጅትም ለመስራት ፈቃደኞች አልሆኑም በማለት ተናግረው፣ “የባቡር ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆኜ እንዲህ የተቸገርኩኝ እዚያ ውስጥ
ያልገባ ሰው ቢሆን ምን ያደርግ ነበር ሲሉ መጠየቃቸውን” ጋዜጣው ዘግቧል። በእግረኞች ማቋረጫ መንገድ ላይ መግባባት አለመቻሉንም
የገለጹት ኢ/ሩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው ጎርፍ ከፊል ምክንያትም ይህ አለመግባባት መሆኑን ጠቅሰዋል። “ከዚህቀደምጐርፉከአንድአካባቢ
ወደሌላመፍሰስይችላል፡፡አሁንግንየባቡር ፕሮጀክቱ ምንም ዓይነት የውኃ ማስወገጃ ሳይተው ግድግዳ በመገንባቱ ውኃውማለፍ
አልቻለም” ሲሉ ባለስልጣኑ ገልጸዋል።