ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግብጽ ከስልጣን በተወገዱት ሙሀመድ ሙርሲ ዳጋፊዎች ላይ የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱትን እርምጃ የሚዘረዝረውንሪፖርት ይፋ
ለማድረግ ካይሮ የተገኙት የሂውማር ራይትስ ወች ዋና ስራ አስኪያጅ ኬኒስ ሮዝና ሌላዋ ከፍተኛ ባለስልጣን ሳራ ሊህ ወደ መጡበት አገር እንዲመለሱ ተደርጓል።
ከ1500 በላይ የተገደሉበትን በአንዳንዶች ዘንድ እንደመፈንቅለ መንግስት የሚታየውን ድርጊት ሂውማን ራይትስ ወች በተደጋጋሚ ሲያወግዝ መቆየቱ ይታወቃል።
የሰብአዊ መብት ድርጀቱ እንዲህ አይነት ድርጊት በግብጽ ምድር ሲፈጸም ለመጀመሪያ ጊዜ
ነው ብሎአል።