ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሪታንያ መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ትኩረት ሰጥታ እንደትከታተለው የሚያሳስቡ የተቃውሞ
ሰልፎች ካለፈው ወር ጀምሮ በእየሳምንቱ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ዛሬ አርብም ለአምስተኛ ጊዜ ተካሂዷል።
ኢትዮጵያውያኑ ስሜታቸውን በከፍተኛ ቁጣ በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ከስፍራው ያነጋገርነው ዘጋቢያችን ወንድማገኝ ጋሹ ገልጿል።
በሌላ በኩል ደግሞ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ግብረሃይል በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳምንት ለአንድ ሰአት ያክል ወደ እንግሊዝ ኢምባሲ ስልክ እንዲደውሉ
እንዲሁም ደብዳቤ እንዲልኩ ጠይቋል። ኢትዮጵያውያኑ የሚልኩት ደብዳቤ በአዘጋጁ ግብረሃይል ተዘጋጅቶ በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን ይለቀቃል።