ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሃምሌ ወር ጀምሮ በከተማው የታየው ከፍተኛ የውሃ እጥረት በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ ደርጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አንድ የከተማው ነዋሪ ውሃ በቦቴ ጭነው አንድ ጀሪካን ውሃ በ10 ብር እየሸጡ ሲሆን፣ አብዛኛው ነዋሪ ደግሞ ወንዝ ውሃ በመጠቀም ችግሩን ለማለፍ እየሞከረ ነው።
” ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነው ያለነው፣ ስለ ንጹህ ውሃ ሳይሆን ውሃ አግኝቶ ጥምን ስለመቁረጥ ነው” የምንነጋገረው በማለት አንድ ነዋሪ የችግሩን አሳሳቢነት ተናግሯል፡፡
ችግሩ በኢሳት እንደቀረበ የከተማው መስተዳድር አንዳንድ እርምጃዎችን ለመውሰድ ቢሞክርም፣ ከቀናት በሁዋላ ተመሳሳይ ችግር መፈጠሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።