ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-50 የሚጠጉ የአፍሪካ መሪዎች በፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ግብዣ በዋይት ሃውስ እንዲሰበሰቡ ቢደረገም፣ አለማቀፍ እውቅና ያላቸው
የመገናኛ ብዙሃን ብዙም ለጉባኤም ትኩረት አለመስጠታቸውን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።
አንድ ከአፍሪካ ውጭ ያለ መሪ አሜሪካን ሲጎበኝ የሚሰጠውን የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን ያክል 50 የአፍሪካ መሪዎች ተደምረው ሊያገኙ አልቻሉም። ቢቢሲ ከአንድ መለስተኛ ዘገባ በስተቀር
ሌሎች ዘገባዎችን ያላስተናገደ ሲሆን፣ ሲኤን ኤን የአፍሪካ መሪዎች ኢባላ የተባለውን ቫይረስ ወደ አሜሪካ ይዘው እንዳይመጡ ያለውን ስጋት ከሚገልጽ መለስተኛ አስተያየት ውጭ በቂ የዜና
ሽፋን አልሰጠውም።
የተሻለ የዜና ሽፋን የሰጠው ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ የኢትዮጵያውያንን ተቃውሞ በጉልህ ዘግቦታል። የጋራ ጥምረት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የተባለው ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ
ፕ/ት ኦባማ ከጨቋኝ የአፍሪካ መሪዎች ጋር ለስብሰባ መቀመጣቸውን የተቹበት ንግግር በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ተስተናግዷል። ከአፍሪካ መሪዎች ተቃውሞ የገጠማቸው የኢትዮጵያና የኮንጎ
መሪዎች ብቻ መሆናቸውንም በዘገባው ተመልክቷል።