ሐምሌ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከአገር ቤት በተከታታይ የሚደወሉ ስልኮችን ለማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት እየገለጸ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች አቶ ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውን ከበሬታ የሚገልጹና ኢህአዴግን በሃይል ለማንበርከክ የሚታገሉትን ቡድኖች ለመቀላቀል እንዴት እንደሚቻል የሚጠይቁ ናቸው።
በሌላ ዜና ደግሞ የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የተፈጸመውን የአፈና ተግባር አውግዟል።
ትህዴን ” የወያኔ አምባገነን ስርአት ህዝቡን እየጨፈጨፈና ለነፃነት የቆሙትን ቁርጠኛ ታጋዮች በመግደል ፣ የህዝቡን የትግል ማእበል መግታት እንደማይቻል ካለፉት አባቶቹ መማር አልቻለም” ካለ በሁዋላ፣ ትናንት በወያኔዎች ቀጥተኛ መሪነት ይካሄድ በነበረውና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች ለጭቁኑ ህዝብ ሲሉ በጠላት ስር የወደቁና ባውደውጊያ ፊት ለፊት ተዋግተው መስዋእትነት በመክፈላቸው ፣ ህዝባዊ ትግሉ በበለጠ እልህና ቆራጥነት ሲቀጥል እንጂ ፣ በከፈለው መስዋእትነት ተደናግጦና ተስፋ ቆርጦ ትግሉ ወደ ኋላ ሲመለስና ትርጉም የለሽ ሲሆን አልታየም” ብሎአል።
መግለጫው ” የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ት.ህ.ዴን/ ይህ በየመን መንግስት በታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ የተፈፀመው ታሪካዊ ስህተት በሁሉም የኢትዮጵያ ጭቁን ህዝቦች ላይ የተፈፀመ እንደሆነ በማመን እኩይ ተግባሩን በፅኑ ያወግዘዋል ” ብለኦል።
“ይህ የታጋይ አንዳርጋቸው ፅጌ ለህዝብ ብሎ የከፈለው መስዋእትነት ደግሞ ያለፉት ጀግኖች አላማቸውን አምነው ለህዝብና ለሃገር ብለው እየከፈሉት የመጡትን ከባድ የመስዋእትነት ዋጋ በመከተል ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ የአንዳርጋቸው ፅጌና የሚሊዮኖች ታጋዮች ዋጋ የከፈሉለት ትግል ወደ ድል ለማብቃት ፣ ትግሉ እንዲጠናከርና የአምባገነኑ ስርአት እድሜ እንዲያጥር ሁሉም በዚህአጋጣሚትግሉን እንዲቀላቀል” ትህዴን ጠይቋል።