ሰኔ ፳(ሃያ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጦርነት ውስጥ የምትገኘዋ ዩክሬን፣ ጆርጂያና ሞልዶቫ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱ አገሮቹን በሂደት የህብረቱ ሙሉ አባል ያደርጋቸዋል። የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን ውሳኔውን አጥብቀው ሲቃወሙት፣ ስምምነቱ አገሮቹን ከሁለት እንደሚከፍላቸው አስጠንቅቀዋል።
አዲሱ የዩክሬን መሪ ስምምነቱን ታሪካዊ ሲሉ አወድሰውታል። የአውሮፓ ህብረት ካውንስል ፕሬዚዳንት ቫን ሮምፑይ በበኩላቸው ስምምነቱ ለአውሮፓ ታላቅ ድል ነው ብለዋል።