ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በበግምብ ገበያ አዳራሽ ውስጥ በጨርቃጨርቅ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ100 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ስራ ያቆሙት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ግብር እንድንከፍል ተጠይቀናል በሚል ምክንያት ነው። ነጋዴዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከደረጃ ሐ ወደ ደረጃ ለ እንዲሸጋገሩ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንዲከፍሉ መታዘዛቸውን ለመቃወም ነጋዴዎቹ ወደ አዋሳ አምርተዋል። የክልሉ ባለስልጣናት ለነጋዴዎቹ ጥያቄ የሰጡት መልስ አልታወቀም።
5 ነጋዴዎች ከግብር ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሲሆን፣ ሌሎች ከ80 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንዲታሰሩ ትእዛዝ መተላለፉን ነጋዴዎች ገልጸዋል።
ነጋዴዎች እንደሚሉት የዞኑ ባለስልጣናት የአካባቢው ተወላጅ ባልሆኑ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ተጽአኖ በመፍጠር አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ እያደረጉ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ የዞኑን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሰካም።