ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢሳት ስልክ በመደወል እንደገለጹት ከቃጠሎው በሁዋላ በከተማው የሚታየው ድባብ አስፈሪ ነው።
በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከመስተዳድሩ ምንም አይነት የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት አለመቻላቸው የህዝቡ ቁጣ እንዲጨምር አድርጎታል።
በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠረውን ንብረት ያወደመውን እሳት የመስተዳድሩ ባለስልጣናት ሆን ብለው አስነስተውታል በሚል ትችት እየቀረበባቸው ነው። መስተዳድሩ በአፋጣኝ ለወደመው ንብረት ተገቢውን ግምትና ካሳ ካልሰጠ ለአመታት የተጠራቀመው ብሶት ወደ አላስፈላጊ ግጭት ሊያመራ ይችላል በማለት ነዋሪዎች እያስጠነቀቁ ነው።
ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው ለአመታት በክልሉ ያለው የስልጣን አወቃቀር ” የማንነት ጥያቄን በማስነሳት ወደ ግጭት” ሊወስድ የችላል በማለት ያስጠነቅቃሉ
ቃጠለውን ተከትሎ ተቃውሞ አሰምተዋል የተባሉ ከ30 እስከ 40 የሚደርሱ ወጣቶች እስር ቤት ተልከዋል። የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት የታሰሩ ሰዎች መኖራቸውን ቢያምኑም፣ ቁጥራቸውን ግን ይፋ አላደረጉም።