የካርቱም ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ጀመሩ

ማጋቢት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ200 ያላነሱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በዳርፉር የተነሳውን ግጭት በመቃወም ወደ አደባባይ ሲወጡ ፖሊስ በሃይል ለመቆጣጠር ሙከራ አድርጓል።

አንድ ተማሪ መሞቱንና ሌላ አንድ ተማሪ መቁሰሉን ዘገባዎች ያመለክታሉ። ተማሪዎቹ ከግቢያቸው ለመውጣት አደረጉት ሙከራ በፖሊስ ቁጥጥር ሲል እንዲውል መደረጉን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን የሚቃወሙ ታጠቂዎች ጋብ ብሎ የነበረውን የዳርፉር ግጭት መጀመራቸው ታውቋል። በአለማቀፍ ፍርድ ቤት የሚፈለጉት ፕ/ት አልበሽር ተደጋጋሚ ተቃውሞዎች እየገጠሙዋቸው ነው። ተቃዋሚዎቻቸውን በአስተዳደሩ ውስጥ ለማሳተፍ እንቅስቃሴ ጀመሩት አልበሽር፣ በአገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር ባለመቻላቸው ስልጣናቸውን ለረጅም ጊዜ አስጠብቀው ለመጓዝ ብዙ ፈተናዎች ከፊታቸው መደቀኑን ተንታኞች ይናገራሉ።