የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማጺው መሪ ሪክ ማቻር እና በ ፕሬዚዳንት ሳል ቫኬር ያለው ልዮነት እየስፋ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ::
ከትላንት በስትያ በነዳጅ የበለጸገችው የአፐር ናይል ስቴት ዋና ከተማ ማላካል ከባድ ጦርነት ተካሂዷል። ወደ ማላካል የሚደረጉ የአየር በረራዎችች መሰረዛቸውንና አካባቢው በከባድ ጦርነት ውስጥ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሎል:: ማላካል የተባለው ቦታ ጠንካራ ስትራቴጅክ ቦታ ሲሆን ይህን ቦታ መቆጣጠር የነዳጅ ቦታዎችን ለመያዝ ያመቻል::
ጦርነቱ ዋራብ ወደ ተባለ ሌላዋ የደቡብ ሱዳን ከተማ እየተዛመተ ሲሆን አንዳንድ አለማቀፍ ድርጅቶችም ሰራተኞቻቸውን በማስወጣት ላይ ይገኛሉ::
የካባቢው ግጭት ያሳሰባት ዑጋንዳ ጦርዋን በማስገባት የ ፕሬዘዳንት ሳልቫክርን መንግስት እየረዳች ሲሆን ፕሬዚዳንት ሙሰቨኒም በትላትናው እለት የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ መግባታቸው ታውቋል::
ዑጋንዳ የደቡብ ሱዳንን መንግስት ለመርዳት የወሰነችው በሚልዮን ዶላር የሚገመት የንግድና የጸጥታ ጥቅሜ ይነካል በማለት ሲሆን የደቡብ ሱዳን አማጽያን ግን ይህንን ፈጽሞ አይቀበሉትም::
በደብረዘይት ከተማ እየተካሄደ ባለው ድርድር አንዱ ችግር የሆነው የዑጋንዳ ጦር አካባቢውን ለቆ አለመውጣቱ ሲሆን ፣ ዑጋንዳ በበኩሏ የአፍረካ ሰላም አስከባሪ እንደገባ ለቅቄ እወጣለው በማለት እንደምክንያት እያቀረበች ነው። የኢጋድ አገሮች ግን የኡጋንዳ ጦር ባለመውጣቱ ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ መቸገራቸውን በመናገር ላይ ናቸው::
በሌላም በኩል ደግሞ ያማጺውን ቡድን ይረዳሉ የሚባሉ አገሮች ማንነት እያነጋገረ ሲሆን አብዛኛዎቹ የኑዌር ጎሳዎች ከኢትዮጵያ ሲሆኑ በደቡብ ሱዳን ያሉ ጎሳዎች ማለትም የሳልቫኪር ደጋፊ የሆኑ በዲንቃ ጎሳዎችና በአማጺው መሪ ደጋፊ በሆኑት የንዌር ጎሳዏች መሃከል ያለው ግጭት ለኢትዮጵያም ሊተርፍ ይችላል የሚሉ ወገኖች እየጨመሩ መተዋል::
በማላካል ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መዘረፉ ጦርነቱ ኢትዮጵያንም ሊጨምር ይችላል የሚለውን አስተያየት አጠንክሮታል።
ኣንዳንድ በደቡብ ሱዳን የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ምንጮች የአማጺው ቡድን ከኢትዮጵያ የደህንነት መስሪያ ቤት የመሳሪያና የሰው ሃይል እርዳታ ያገኛል ብለው በመናገር ላይ ሲሆኑ ፣ የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋምና በየአገሩ ያሉ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቲክ ሰራተኞች ግን የኤርትራ መንግስትን በመክሰስ የኢሳያስ መንግስት በአውሮፕላን ከአስመራ ተነስቶ በኢትዮጵያ በማቆራረጥ አማጽውን መሪ የሬክ ማቻርን ጦር ይረዳል በማለት እየተናገሩ ናቸው::
የአሜረካ መንግስት በትላንትናው እለት ባወጣው መግለጫ ሁለቱም ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዲያከብሩ የገለጸ ሲሆን ችግሩም ወደ ሌላ አገሮች እንዳይዛመት አሳስቧል።