የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዕምሮ ቸግር ፤ ዘገምተኝነት ፤ ሱስ ፤ ራስን መጣል ፤ የስነ ልቦና ችግር ፤ድብርት ፤ ከሰው መገለል፤ተስፋ መቁረጥ ፤ እራስን ማጥፋት ፤ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግሮች፤ አሰገድዶ መደፈር ችግር የጣላባቸው ጠባሳ በህይወታቸው ላይ ከባድ ተጽኖ ሁኖ ይሰተዋልባቸዋል ሲል የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስጠናው ጥናት አመልክቷል፡፡
ከአርባ ሃገራት ሰደተኛቸ ተመላሺ ኢትዩጵያውያን የኢትዩጵያን መሬት በረገጡ በሳልስቱ ጀምሮ የማቋቋሚያ 1800 ብር ይዘው በሱዳን ገዳሪፍ በኩል በህገ ወጥ መጉረፍ የጀመሩት ተይዘው በድጋሜ የተመለሱት እንዳሉ በፖሊስ መረጃ ሚኒስተሩ አረጋግጫለሁ ብለዋል፡፡የመተማ ፖሊስም ሊጠፉ ሲሉ 3 ሺ 242 ተመላሺ ሰደተኞች መያዙን በማየት ቦሌ አየር ማረፊያ አርፈው መተማ ለመሄድ ትኬት ሲቆርጡ እንዴት ዝም ተባሉ ሲል ይጠይቃል።
በመተማ እየሱስ የሃገር ውስጥ ድህነትን ፈርተው በመሸሺ ወደ ሱዳን እና አረብ ሃገራት የሚሰደዱት ቁጥር በቀን 1ሺ 800 የሚገመት ሲሆን ራሳቸውን ስተው በእብደት ደረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንዳሉ እንዲሁም ባዶ እጃችንን አንመለስም በማለት በሴተኛ አዳሪነት የድንበር ከተማዋን ከበው በቀን በ10 ብር እና 20 ብር ገንዘብ የሴተኛ አዳሪ ህይዎት በሱዳናዊያን ዜጎች እየተደፈሩ እንደሚኖሩ መረጃዎች ያመለክታሉ።
3 ከስደተኝነት የተመለሱ ኢትዩጵያውያን በተስፋ መቁረጥ ሃገር ቤት በገቡ በቀናት ጊዜ ውስጥ እራሳቸውን ማጥፋታቸው ታውቋል፡፡