በቫንኩቨርና ሙኒክ የእርዳታ ገንዘብ ተሰበሰበ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፌብሩዋሪ 18//2014 በኤድመንድ ኮሚዩኒቲ ማእከል አዳራሽ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የቫንኮቨር ነዋሪዎች በመገኘት የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ አበርክተዋል።

የእርዳታ አሰባሳቢው ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት አቶ ደበበ ጉሉ ያቀናበሩት፤ በአረብ አገሮች የተከሰተውን የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የሚያሳዩ የቪዲዮ ቅጂዎች በዝግጅቱ ላይ ለእይታ በመቅረባቸው የወገኖቻቸውን ስቃይ በፊልሙ የተመለከቱ ታዳሚዎች ልባቸው በሀዘን ተነክቶ አንዳንዶች ማምሻውን ሲያለቅሱ ተስተውልዋል። በዝግጅቱ ላይ 10 ሺ የካናዳ ዶላር መገኘቱም ታውቋል።