የካቲት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮሚያ ክልል በቡሌ ሆራ ወረዳ፣ በሀገረማርያም ከተማ ከአርሴማ ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ የተነሳውን የውስጥ ችግር ተከትሎ ችግሩን ለመፍታት የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ አባላት ታስረው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ከተጠየቀባቸው በሁዋላ ህዝቡ ባሰማው ከፍተኛ ተቃውሞ የአገር ሽማግሌዎቹ በዛሬው እለት የተፈቱ ሲሆን፣ ህዝቡ በድል አድራጊነት ስሜት በሆታ አጅቦ ወደ ቤተክርስቲያን ወስዷቸዋል።
የአገር ሽማግሌዎቹ ትናንት ረቡእ እንዲፈቱ መንግስት ፈልጎ የነበረ ቢሆንም፣ የአገር ሽማግሌዎች ግን ፍርድ ቤት ቀርበን ጥፋታችን ሳይነገረን አንፈታም በማለታቸው ዛሬ ያለቀጠሮአቸው ቀርበው እንዲፈቱ ተደርጓል።
ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው አቡነ ገብርኤል የአገር ሽማግሌዎቹ እንዲፈቱ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገሩና ሲመካከሩ ውለዋል።
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት የናጋገርናቸው ተሳታፊዎች እንደገለጹት ጳጳሱና የአገር ሽማግሌዎች በቤተከርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኝተዋል